ተረት አና ግጥሞች

አቤት ማማሯ

የናቱዬ ድመት አቤት ማማሯ
በቀለማት ተዥጎርጉራ ተዥጎርጉራ።

ፀሐይ የመሰለ ቢጫ ፊት ነው ያላት
ከቀይ ጢሟ ጋር በጣም ነው የሚያምርባት።

እንደ ውቅያኖስ ውሃ ኩልል ጥርት ያሉ
ሰማያዊ አይኖችዋ ከብለል ከብለል ሲሉ
ያላፊ አግዳሚውን ልብ ይማርካሉ።

አረንጓዴ ጆሮዎቿ ግራ ቀኙን ይዘው
እንደ አንቴና ተወጥረው
አናቷ ላይ የበቀሉ
ቅጠል ነገር ይመስላሉ።

በጀርባዋ በኩል ካንገቷ ጀምሮ
እስከ ታች ድረስ ጭራዋን ጨመሮ
ቀለሟ ጥቁር ነው
ጃኖ ነው የሚመስለው።

በሆዷ በኩል ግን ገልብጠን ስናያት
ጥጥ የመሰለ ነው ነጭ ፀጉር ያላት።

ቡኒ እግሮቿን .. ለተመለተው
ሕብረ ቀለሙ እጅግ .. የሚማርክ ነው
ስትዘል ስትቧርቅ እያንጸባረቀ
የስንቱን ተመልካች ልቦና ሰረቀ።

የናቱዬ ድመት አቤት ማማሯ
በቀለማት ተዥጎርጉራ ተዥጎርጉራ።


ምንጭ:
አሌኒ ፀጋዬ
መጀመሪያ |ወደ ሚቀጥለው