ተረት አና ግጥሞች

የምትጠጣው ወተት

የናቱዬ ድመት
የምትበላው ዳቦ የምትጠጣው ወተት
ምትተኛው ማታ ምትነሳው ጠዋት።

ጠዋት ስትነሳ
እጇን ልሳ ልሳ
ፊቷን አብሳ
መላልሳ መላልሳ
አጇን ልሳ ልሳ።

ሚያው ብላ ሰላምታ
በቋንቁዋ ሰጥታ
ወተቱ እስኪታለብ እየጠበቀች፡
ቁርሷዋን ልትብላ ከገሏ አጠገብ ሄዳ ቁች አለች።

የናቱዬ ድመት
የምትበላው ዳቦ የምትጠጣው ወተት
ምትተኛው ማታ ምትነሳው ጠዋት።

ወተቷን ከፊቷ በምላሷ ልሳ
ስትጠግብ አፏን በአጇ አብሳ
ከዚያም በምልሷ እጇን ልሳ ልሳ
በቋንቁዋ ደግሞ ወዲያው ትደግምና
ሚያው ብላ አምስግና
በፍጥነት እሮጠች
ወደ ጨዋታዋ ተደስታ ሄደች።


ምንጭ:
አሌኒ ፀጋዬ
መጀመሪያ | ወደ ቀደመው